Aster Abebe/Keber Yebeqah Neh/Felegieh

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
    ፈልጌህ ፡ አላጣሁህም 
    ከልቤ ፡ ሽቼህ ፡ ራስህን ፡ አልሰወርክም 
    (፪x)
    ውሃ ፡ በሌለበት ፡ በደረቅ ፡ ምድር 
    ነፍሴ ፡ ተጠምታ ፡ አገኘችህ ፡ 
    አገኘችህ  (አገኘችህ) ፪x
    በቅቤና ፡ በስብ ፡ እንደሚረካ ፡ ሰው 
    ሳገኝህ ፡ ልቤን ፡ ደስ ፡ አለው (፪x)


    ተመችቶኝ ፡ ነው ፡ አባትነትህ 
    ዘላለም ፡ በቤቴ ፡ እራስ ፡ ሁን ፡ የምልህ 
    ተመችቶኝ ፡ ነው ፡ አምላክነትህ 
    ዘላለም ፡ በላዬ ፡ ንገስብኝ ፡ ምልህ


    አዛኝ ፡ ባትሆን ፡ ፍቅር ፡ ባትሆን ፡ 
    አምላኬ ፡ ባትሆን ፡ ጌታዬ ፡ ባትሆን 
    ባትሸከመኝ ፡ በፍቅር ፡ ባትይዘኝ ፡ 
    ፈቅደህ ፡ ባትምረኝ ፡ መክረህ ፡ ባትመልሰኝ 


    በፍቅር ፡ ባትይዘኝ ፡ ፈቅደህ ፡ ባትምረኝ ፡
    ምክርህ ፡ ባይደግፈኝ 
    ምን ፡ ይሆን ፡ ነበረ ፡ ዕጣዬ
    ስለምሕረትህ ፡ ተመስገን ፡ ጌታዬ (2x)


    አቅም ፡ የሆንክልኝ ፡ ተባረክ 
    ዘውዴ ፡ መድመቂያዬ ፡ ተባረክ 
    ቅድስናዬ ፡ ነህ ፡ ተባረክ 
    አብ ፡ ፊት ፡ መታያዬ ፡ ተባረክ 
       (፪x)
    ተባረክ ፡ ተባረክ ፤ ተባረክ ፡ ተባረክ 
    ተባረክ ፡ ተባረክ ፤ ተባረክ ፡ ተባረክ
    እኔ ፡ ምፈልገው ፡ (አንተን ፡ ነው) (፫x)
    ሌላው ፡ በሙሉ (ቀሪ ፡ ነው) (፫x) 
    ሁሌ ፡ ምናፍቀው (አንተን ፡ ነው) (፫x) 
    ሌላው ፡ በሙሉ (ቀሪ ፡ ነው) (፫x)


    እኔ ፡ ምፈልገው ፡ አንተን ፡ ነው 
    ሌላው ፡ በሙሉ ፡ ቀሪ ፡ ነው 
    እኔ ፡ ምፈልገው ፡ አንተን ፡ ነው 
    ሌላው ፡ በሙሉ ፡ (ቀሪ ፡ ነው) (፮x)