From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ይለፈኝ ባለማዕረጉ ይለፈኝ ባለጸጋው
ይለፈኝ አጃቢ ያለው ይለፈኝ ባለጊዜው
ይለፈኝ ያልኩት ወዳጄ ይለፈኝ የበላ ከእጄ
ይለፈኝ ዘመዴ ያልኩት ገበናዬን ገልጬ ያሳየሁት
አትለፈኝ በቃልህ አትለፈኝ ኢየሱሴ
አትለፈኝ ሳትነካኝ አትለፈኝ መጽናኛዬ
መንፈስህ ሳይነካኝ አትለፈኝ ይህቺ ቀን
ፈቃድህ ሳይፈጸም አትለፈኝ ይህች ቀን
ቃልህ ሳይበራልኝ አትለፈኝ ይህች ቀን
የልብህን ሳትነግረኝ አትለፈኝ ይህች ቀን
አትለፈኝ በቃልህ አትለፈኝ ኢየሱሴ
አትለፈኝ ሳትነካኝ አትለፈኝ መጽናኛዬ
መንፈስህ ሳይነካኝ አትለፈኝ ይህቺ ቀን
ፈቃድህ ሳይፈጸም አትለፈኝ ይህች ቀን
ቃልህ ሳይበራልኝ አትለፈኝ ይህች ቀን
የልብህን ሳትነግረኝ አትለፈኝ ይህች ቀን
በፍቅርህ የተገፉትን የምታቀርብ
በትከሻህ የዛሉትን የምትሸከም
በክንፎችህ ታናናሾችን ትይዛለህ
በርህራሄ አይኖችህ የተጣለውን ታነሳዋለህ
በፍቅርህ የተገፉትን የምታቀርብ
በትከሻህ የዛሉትን የምትሸከም
በክንፎችህ ታናናሾችን ትይዛለህ
በርህራሄ አይኖችህ የተጣለውን ታነሳዋለህ
ጣትህ ፈውስ ነው ህመም ለጠናበት
ቃልህ ሰላም አለው ሃዘን ለገባው ቤት
በብር እና በወርቅ ሳይሆን አንተን ሰምቶ ስንቱ አረፈ
በበዛው ሰላምህ እየተትረፈረፈ
ጣትህ ፈውስ ነው ህመም ለጠናበት
ቃልህ ሰላም አለው ሃዘን ለገባው ቤት
በስጦታህ ብዛት ሳይሆን አንተን ሰምቶ ስንቱ አረፈ
በበዛው ሰላምህ እየተትረፈረፈ
ይለፈኝ ሰው የጓጓለት ይለፈኝ የሚሯሯጥለት
ይለፈኝ ከፍ ብሎ የታየው ይለፈኝ ለስጋ የሆነው
ይለፈኝ የሚመስል ከፍታ የተናቀ በአንተ እይታ
ነገር ግን ከአንተ ለሆነው ይኸው እጄን ከፍ አድርጌአለሁ
አትለፈኝ በቃልህ አትለፈኝ ኢየሱሴ
አትለፈኝ ሳትነካኝ አትለፈኝ መጽናኛዬ
መንፈስህ ሳይነካኝ አትለፈኝ ይህች ቀን
ፈቃድህ ሳይፈጸም አትለፈኝ ይህች ቀን
ቃልህ ሳይበራልኝ አትለፈኝ ይህች ቀን
የልብህን ሳትነግረኝ አትለፈኝ ይህች ቀን
ለቁስል የሚሆን ዘይት በእጅህ አለ
ያልጀመረ በኔ ስንቱን ቤት ያከመ
ዛሬም ከኔ ደርሶ አይቀንስ ጉልበቱ
ፈሶ ያድነኛል ያደርገኛል ብርቱ
ለአንተ ብቻ እንድሆን ካዛለኝ ሸሽቼ
ሃሳቤን መንገዴን ሁሉዬን ሰጥቼ
በደነገለ ህይወት በማይሆን ለሌላ
ሆኜ ልለቅልህ ፈጥነህ አግኘኝና
አትለፈኝ በቃልህ አትለፈኝ ኢየሱሴ
አትለፈኝ ሳትነካኝ አትለፈኝ መጽናኛዬ
መንፈስህ ሳይነካኝ አትለፈኝ ይህች ቀን
ፈቃድህ ሳይፈጸም አትለፈኝ ይህች ቀን
ቃልህ ሳይበራልኝ አትለፈኝ ይህች ቀን
የልብህን ሳትነግረኝ አትለፈኝ ይህች ቀን
|