From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
እስሬን ፡ ጥብቅ ፡ አደረገና
ማረጂያውን ፡ ሳል ፡ አረገና
ጉድጓድ ፡ ምሶ ፡ ሲጠብቀኝ
ቀን ፡ ቀጥሮ ፡ ዋጥ ፡ ሊያደርገኝ
ያመለጠ ፡ እኔ ፡ ነኝ ፡ ያመለጠ (፬x)
እስሬን ፡ ጥብቅ ፡ አደረገና
ማረጂያውን ፡ ሳል ፡ አረገና
ጉድጓድ ፡ ምሶ ፡ ሲጠብቀኝ
ቀን ፡ ቀጥሮ ፡ ዋጥ ፡ ሊያደርገኝ
ያመለጠ ፡ እኔ ፡ ነኝ ፡ ያመለጠ (፬x)
አዝ፦ ያን ፡ ለት ፡ ነው ፡ አድራሻዬ ፡ የተቀየረዉ
ያን ፡ ለት ፡ ነው ፡ ችግር ፡ ለቆኝ ፡ ትቶኝ : የሄደው
ያን ፡ ለት ፡ ነው ፡ ያ ፡ ከሳሼ ፡ ጉድ ፡ የፈላበት
ያን ፡ ለት ፡ ነው ፡ ደጉ ፡ ጌታ ፡ ቤት ፡ የገባበት
ያመለጠ ፡ እኔ ፡ ነኝ ፡ ያመለጠ (፬x)
ከሲኦል ፡ መትረፌ ፡ በኢየሱስ ፡ ማረፌ ፡ ይህ ፡ ካልገረመኝ
ከልዑሉ ፡ ጋራ ፡ በቀኝ ፡ መቀመጤ ፡ ካላስጨፈረኝ
ታዲያ ፡ ምን ፡ ይግረመኝ ፡ ከመትረፌ ፡ ሌላ ፡ ምን ፡ ያስጨፍረኝ
ደሙን ፡ ከፍሎ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የሕይወቴ ፡ ጌታ ፡ ኧረፍት ፡ የሰጠኝ
አዝ፦ ዛሬም ፡ ይግረመኝ ፡ እንጂ ፡ ነገም ፡ ይግረመኝ
በእርሱ ፡ አይደለም ፡ ወይ ፡ ችግሬ/ጨለማው ፡ እጁን ፡ ያሰጠኝ (፪x)
ያመለጠ ፡ እኔ ፡ ነኝ ፡ ያመለጠ (፬x)
ያመለጠ ፡ እኔ ፡ ነኝ (፬x)
በጣም ፡ ደካማ ፡ ሰው ፡ ሸክም ፡ ያጐበጠኝ ፡ የከበደብኝ
እንዲያው ፡ ወዶኝ ፡ እንጂ ፡ መዳን ፡ ያልተገባኝ ፡ ሙት ፡ ሰው ፡ ነበርኩኝ
መች ፡ ምህረት ፡ ወድጄ ፡ ወይስ ፡ እሮጬ ፡ ነው ፡ ይህ ፡ የሆነልኝ
የቀደሰኝ ፡ ጌታ ፡ መርገሜን ፡ ሻረና ፡ በሕይወት ፡ ኑሪ ፡ አለኝ
አዝ፦ ዛሬም ፡ ይግረመኝ ፡ እንጂ ፡ ነገም ፡ ይግረመኝ
በእርሱ ፡ አይደለም ፡ ወይ ፡ ችግሬ/ጨለማው ፡ እጁን ፡ ያሰጠኝ (፪x)
ያመለጠ ፡ እኔ ፡ ነኝ ፡ ያመለጠ (፬x)
እኔ ፡ ነኝ (፬x)
ዘንዶ ፡ የተወጋልኝ ፡ እሳቱ ፡ የጠፋልኝ
ከአፈር ፡ የተነሳሁኝ ፡ ጌታ ፡ ሞገስ ፡ የሆነኝ
ዘንዶ ፡ የተወጋልኝ ፡ እሳቱ ፡ የጠፋልኝ
ከአፈር ፡ የተነሳሁኝ ፡ ጌታ ፡ ሞገስ ፡ የሆነኝ
አዝ፦ ያመለጠ ፡ እኔ ፡ ነኝ ፡ ያመለጠ (፬x)
|