እሰጥሃለሁ ሕይወቴን (Track 8 Adane Asnake Mamo) - ጆይፉል ሳውንድ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ጆይፉል ሳውንድ
(Adane Asnake Mamo)

Lyrics.jpg


(1)

በመስቀል የሞተው
(Bemeskel Yemotew)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፯ (2014)
ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 6:13
ጸሐፊ (Writer): አዳነ አስናቀ ማሞ
(Adane Asnake Mamo
Property "Writer" has been marked for restricted use.
)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የጆይፉል ሳውንድ ፡ አልበሞች
(Albums by Adane Asnake Mamo)

እሰጥሃለሁ ሕይወቴን እሰጥሃለሁ ዘመኔን
እሰጥሃለሁ ዕድሜዬን ለአንተ ለአምላኬ
ሳልሰጥህ የኔ ብዬ የማስቀረው ምንም የለኝ
ነፍሴን መንፈሴን ስጋዬን አስረክባለሁኝ

በእጆቼ ሰርቼ የማገኘውን ገንዘቤን
በጥረት ያገኘሁት ዕውቀቴን
በተፈጥሮ የተሰጠኝ ችሎታዬን
እንካ ውሰደው እሰጥሃለሁ ለአንተ ለጌታዬ

የሕይወቴ መሪ አልሆንም አኔ ለራሴ
አልንበረከክም ለስሜቴ
የአንተ ብቻ ነኝ ኢየሱስ ጌታ
ይሄው ማንነቴ ለአንተ ያለኝ ስጦታ

እንካ እኔን እንካ ውሰድ ራሴን ውሰድ
ለክብርህ እኖራለሁ ጽድቅህን እገልጣለሁ
ልሁን የኪስ ገንዘብህ ስራብኝ ልኑርልህ

ጠብቀኝ ከስሜቴ
ጠብቀኝ ከምኞቴ
ጠብቀኝ ከፈቃዴ