ጓደኛ ምን ያህል ይቀርባል (Track 6 Adane Asnake Mamo) - ጆይፉል ሳውንድ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

https://www.youtube.com/watch?v=uQAy6i87Cm0&list=PLvd6Ao9nWjlx8WI8reelS1yPGnyP_KgtX&index=6

ጆይፉል ሳውንድ
(Adane Asnake Mamo)

Lyrics.jpg


(1)

በመስቀል የሞተው
(Bemeskel Yemotew)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፯ (2014)
ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 5:29
ጸሐፊ (Writer): አዳነ አስናቀ ማሞ
(Adane Asnake Mamo
Property "Writer" has been marked for restricted use.
)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የጆይፉል ሳውንድ ፡ አልበሞች
(Albums by Adane Asnake Mamo)

ጓደኛ ምን ያህል ይቀርባል
ወዳጅስ ምን ያህል ይጠጋጋል
የልቤን የውስጤን ማን ይረዳል
ሐሳቤንስ ማን ይመረምራል

ኢየሱስ መድህኔ አምላኬ አንተ ግን
ከወዳጅ ይልቅ ትጠጋጋለህ
ከእስትንፋሴ ይልቅ ቅርቤ ነህ
የውስጤን ምትረዳ ንግግሬ የሚገባህ
ምኞቴን ሐሳቤን ዘልቀህ የምታየኝ
የማመልክህ ኢየሱስ ቅርቤ ነህ

የማይደረስ ጥልቅ ሐጀሳቤን ታየዋለህ
ድምጽ የሌለው የውስጥ ጩሄቴን ትሰማለህ
ልትለውጠው ከንቱነቴን ትመጣለህ
ልቤን ለክብርህ እንደ ቃልህ ትቀርጻለህ

ብቻዬን የሆንኩኝ ሲመስለኝ አብረሄኝ ነህ
ሕይወት ትግል ሲሆንብኝ ረዳቴ ነህ
ተስፋዎቼ ሲጨልሙ አንተ ተስፋ ነህ
ኢየሱስ ሁልጊዜ ከኔ ጋር ነህ