ኢየሱስ ከስም ሁሉ በላይ (Track 5 Adane Asnake Mamo) - ጆይፉል ሳውንድ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ጆይፉል ሳውንድ
(Adane Asnake Mamo)

Lyrics.jpg


(1)

በመስቀል የሞተው
(Bemeskel Yemotew)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፯ (2014)
ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 3:45
ጸሐፊ (Writer): አዳነ አስናቀ ማሞ
(Adane Asnake Mamo
Property "Writer" has been marked for restricted use.
)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የጆይፉል ሳውንድ ፡ አልበሞች
(Albums by Adane Asnake Mamo)

ኢየሱስ/2 ከስም ሁሉ በላይ ኢየሱስ/3 ከሁሉ በላይ

ከሰማይ ሰማያት ከታላቅ ስፍራ
ዝቅ ብሎ ተገኘ ሊኖር ከኔ ጋራ
በላይ ካለው ክብር ከግርማውም ይልቅ
እጅግ በለጠበት ለኔ ያለው ፍቅር ከዚህ የተነሳ/2
እግዚአብሔር ከፍ ከፍ አረገው
ከስም በላይ ያለውን ስም ሰጠው

አጋንንት ለስሙ ያታዘዙለታል
የምድር ፍጥረታት ድምጹን ይሰሙታል
ሁሉንም ይገዛል በስራው ታላቅ ነው
ተዓምርን ይሰራል ስሙ ጉልበታም ነው እኛም በምድር ያለን/2
ስሙን በእምነት እንጠራለን ኢየሱስ/2 እንላለን

ሐያላን አልፈዋል እንዲሁም ነገስታት
ስማቸው ተረስቶ ሆኗል ተረት ተረት
ክፉ ቀን ሲመጣ መች ቆሙ በርትተው
ከነታሪካቸው ሞት አሸነፋቸው የኛ ኢየሱስ ግን/2
ሞት እንኳን ከቶ አልቻለውም
በክብር ከፍ ብሏል ለዘላለም