እጆችህ ሰሩኝ (Track 3 Adane Asnake Mamo) - ጆይፉል ሳውንድ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ጆይፉል ሳውንድ
(Adane Asnake Mamo)

Lyrics.jpg


(1)

በመስቀል የሞተው
(Bemeskel Yemotew)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፯ (2014)
ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 4:13
ጸሐፊ (Writer): አዳነ አስናቀ ማሞ
(Adane Asnake Mamo
Property "Writer" has been marked for restricted use.
)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የጆይፉል ሳውንድ ፡ አልበሞች
(Albums by Adane Asnake Mamo)

እጆችህ ሰሩኝ በአጃጁኝ በቃልህ ተፈጠርኩ
ምህረትህ ለመጽናናቴ ሕግህ ደግሞ ተድላዬ
ሃሌሉያ ሃሌሉያ ቃልህ አውነት ነው አሜን/2

ሕግህ ለእግሬ መብራት ለመንገዴም ብርሃን ነው
እውነትን ያወኩበት የልቤ ደስታ ነው
ከማር ከወለላ ቃልህ ይጣፍጣል
የዘለዓለም ጽድቅ የሕይወት ምንጭ ይሆናል

ከአንተ ወዴት ሄዳለሁ የሕይወት ምንጭ ነህ
ከአንተ ወዴት ሄዳለሁ የሕይወት ውሃ ነህ ውሃ

ሕያው የሆንኩበት የበረታሁበት
ጽድቅን ያየሁበት ከሞት የዳንኩበት
ጌታ ሆይ ቃልህ ነው ዛሬን የቆምኩበት
ጥጋብ እርካታዬ ብርሃን ያየሁበት

ከአንተ ወዴት ሄዳለሁ የሕይወት ምንጭ ነህ
ከአንተ ወዴት ሄዳለሁ የሕይወት ውሃ ነህ ውሃ

ተድላዬ ቃልህ ነው ከክፉ የጠበቀኝ
ሕግህን ስማር መንፈስህ የነካኝ
የማይጠፋ ታሪክ በልቤ የተጻፈው
ሕይወትን የሚሰጥ የቃልህ እውነት ነው