እግዚአብሔር ረዳቴ (Track 2 Adane Asnake Mamo) - ጆይፉል ሳውንድ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ጆይፉል ሳውንድ
(Adane Asnake Mamo)

Lyrics.jpg


(1)

በመስቀል የሞተው
(Bemeskel Yemotew)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፯ (2014)
ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 4:13
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የጆይፉል ሳውንድ ፡ አልበሞች
(Albums by Adane Asnake Mamo)

እግዚአብሔር ረዳቴ መሸሸግያ አለቴ መድህኔ
ምርኩዝ ለሕይወቴ መከታ ጋሻዬ አለኝታዬ
በለመለመ መስክ ሁሌ ያሳድረኛል ይመራኛል
ይመራኛል/5

ምድር ብትናወጥ ተራሮች ቢቀልጡም ልቤ አይፈራም
እርሻው መብል ባይሰጥ ከብቶችም ባይኖሩ ከቶ አልሰገፋም
የኔ መኖርያዬ እግዚአብሔር ብቻ ነው ተስፋዬ ነው
ተስፋዬ ነው/5

እንደ ሐያል እና ደግሞ እንደ ጨካኝ ከጎኔ ነው
ታድያ የሚያስፈራኝ የሚያስደነግጠኝ ከቶ ማን ነው
በወጀብ ማዕበል መንገድ አለው ጌታ ይረዳኛል
ይረዳኛል/5

ልቤን ደስ ይለዋል እርሱን ባሰብኩ ቁጥር እጽናናለሁ
ሐዘኔን ብሶቴን መከራዬን ሁሉ እረሳለሁ
ከፍቅሩ የተነሳ አድኖኛል እና ይወደኛል
ይወደኛል/5