የነፍሴ እረፍቷ (Track 14 Adane Asnake Mamo) - ጆይፉል ሳውንድ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ጆይፉል ሳውንድ
(Adane Asnake Mamo)

Lyrics.jpg


(1)

በመስቀል የሞተው
(Bemeskel Yemotew)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፯ (2014)
ቁጥር (Track):

፲ ፬ (14)

ርዝመት (Len.): 5:13
ጸሐፊ (Writer): አዳነ አስናቀ ማሞ
(Adane Asnake Mamo
Property "Writer" has been marked for restricted use.
)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የጆይፉል ሳውንድ ፡ አልበሞች
(Albums by Adane Asnake Mamo)

የነፍሴ እረፍቷ ደግሞም ጉብኝቷ ከሰማይ ነው

ከምድር ጭቃ አበጅቶኝ እስንፋሱን እፍ ሲልብኝ
ያን ጊዜ ሕያው ሰው ሆንኩኝ አገኘሁኝ ሕይወትን
ስጋዬ ቢሆን ከአፈር ነፍሴ ግን እስንፋሱ ነች
የምድር ከቶ ያልሆነች ከእግዚአብሔር የተገኘች

ስጋ ወደ አፈር ይሄዳል መገኛው ይሄው ነውና
ነፍሴም ወደ መጫችበት ትሄዳለች ወደ አምላኳ
ከእግዚአብሔር ስለተገኘች እረፍቷም ከእግዚአብሔር ነው
ምድራዊው ለስጋ ሲሆን የነፍሴ ግን ከሰማይ ነው

ከምድረ የሚገኝ ደስታ ስጋዬን ይሸነግላል
ከሰማይ የሚመጣው ግን ነፍሴን ያሳርፋታል
ከአፉ የሚወጣው ቃል አጥንቴን ዘልቆ ይገባል
ስጋዬንም ተቆጣጥሮ ነፍሴን በምክሩ ያጠግባል

https://www.youtube.com/watch?v=H_kwRqYbEso&list=PLvd6Ao9nWjlx8WI8reelS1yPGnyP_KgtX&index=14