ወደ ደጆቹ በመገዛት (Track 13 Adane Asnake Mamo) - ጆይፉል ሳውንድ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ጆይፉል ሳውንድ
(Adane Asnake Mamo)

Lyrics.jpg


(1)

በመስቀል የሞተው
(Bemeskel Yemotew)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፯ (2014)
ቁጥር (Track):

፲ ፫ (13)

ርዝመት (Len.): 4:09
ጸሐፊ (Writer): አዳነ አስናቀ ማሞ
(Adane Asnake Mamo
Property "Writer" has been marked for restricted use.
)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የጆይፉል ሳውንድ ፡ አልበሞች
(Albums by Adane Asnake Mamo)

ወደ ደጆቹ በመገዛት ወደ አደባባዩ በምስጋና እቀርባለሁ
እሰግዳለሁ ጌታን አከብራለሁ
እቀኛለሁ ለእርሱ ዘምራለሁ እሰግዳለሁ

በበጎ ሕሊና በተቀደሰ ልብ በፊቱ ሁሌ እሆናለሁ
እራሴን ሰጥቼ ልቤን አስገዝቼ ሁልጊዜ ዘምርለታለሁ
ያንስበታል እንጂ አይበዛውምና አምላኬን አከብረዋለሁ
በቀረኝ ዘመኔ እግዚአብሔርን አመልካለሁ

ቸርነቱ ብዙ ምሕረቱ ዘላለም ለልጅ ልጅ ሁሉ ነውና
እርሱን ላመሰግን በፊቱ ልዘምር ልሰዋ ከልቤ ምስጋና
ቅደሳን በፊቱ ተንበረከኩለት ተራሮችም ዝቅ ዝቅ አሉ
ምድርና ሞላዋ ለእግዚአብሔር እልል በሉ

ጽድቁን ያወራሉ ሰማይ እና ምድር አሕዛብም ክብሩን አዩ
ዳርቻዎች ሁሉ የአምላካችንን ማዳኑን ተገነዘቡ
ድምጹን ይሰሙታል እርሱ እንዳዘዛቸው ፍጥረታት ወጥተው ይገባሉ
ክብርና ምስጋና ለጌታቸው ያቀርባሉ
https://www.youtube.com/watch?v=fDb8yNs_X8s&list=PLvd6Ao9nWjlx8WI8reelS1yPGnyP_KgtX&index=13