Tesfaye Chala/Yebelay Neh Gieta/Aderegelegn Teamer

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ርዕስ አደረገልኝ ተዓምር ዘማሪ ተስፋዬ ጫላ አልበም የበላይ ነህ ጌታ

እንዳለፈ ውኃ መከራዬን አስረሳኝ በጠላቶቼ ፊት እራሴን በዘይት ቀባ ኧረ እንዴት ይበዛል ሌት ተቀን ባከብረው ማንም የማይመስለው ወዳጅ አግኝቻለሁ (፬x)

አሃሃ የጠላቴ ዛቻ አሃሃ አይ ማስፈራራቱ አሃሃ ከንቱ ሆኖ ቀረ አሃሃ ቀደመች ምህረቱ አሃሃ ሌሊት በእሳት አምድ አሃሃ በደመና መራኝ አሃሃ እረ ማነው ከልካይ አምላኬ ከረዳኝ እረ ማነው ከልካይ ኤልሻዳይ ከረዳኝ

አዝ አደረገልኝ ተአምር አደረገልኝ (፪x) ተራራዬን ናደው ናደው ሸለቆዬን ሞላ ሃሃ ባሕሩን ከፈለው ኦሆሆ መንገዴን አቀና (፪x)

ዘይት ከማሰሮ ከማድጋው አልቆ ተስፋዬ ተሰብሮ ተሰባብሮ ደቆ ስሙን ተጣርቼ የልቤን ስነግረው እፌን ሞልቶ በሳቅ ሕይወቴን አዳነው የአምናው ችግር ሄደ ማድጋው ሙሉ ነው ከራሴ ተርፌ አለኝ የምሰጠው የታምራት አምላክ ተአምር አድርጐልኛል ፍጥረት ሁሉ ይስማው ነገር ተገልብጧል

አዝ አደረገልኝ ተአምር አደረገልኝ (፪x) ተራራዬን ናደው ናደው ሸለቆዬን ሞላ አሃሃ ባሕሩን ከፈለው ኦሆሆ መንገዴን አቀና (፪x)

አሃሃ አዲስ ቅኔ ላምጣ አሃሃ ላክብረው ሳልቆጥብ አሃሃ እግሮቼም ይዝለሉ በፊቱ ላሸብሽብ አሃሃ ክብሬን ብጥልለት አሃሃ የሚንቀኝ ማነው አሃሃ ያደረገልኝን እኔ ነኝ የማውቀው አሃሃ የተሰራልኝን እኔ ነኝ የማውቀው

ሰማይ ጥርት አለ ደመናውም ጠፋ የችግሩ ብርታት ፊቴን ለቆ ጠፋ የነበረው ሄደ ያለውም አለቀ ውኃ ሳይኖርበት ሸለቆው ደረቀ ደመናም ሳይታይ ንፋስም ሳይነፍስ ዝናባትን አዞ ምድርን ሲያረሰርስ የጠላቴን እቅድ እያፈረሰልኝ ድል በድል ላይ ለመድኩ ድንቅ አደረገልኝ

አዝ አደረገልኝ ተዐምር አደረገልኝ (፪x) ተራራዬን ናደው ናደው ኦሆሆ ሸለቆዬን ሞላ ባሕሩን ከፈለው ኦሆሆ መንገዴን አቀና (፪x)