Tekeste Getnet/Mekniyatie Bezu New/Mekniyatie Bezu New

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ዘማሪ ተከስተ ጌትነት ርዕስ ምክንያቴ ብዙ ነው Volume 2

አንደበቴ ከምስጋና በቀር ሌላ አያውቅም

ይዘምራል ላንተ ክብር ሰለቸኝ አይልም

ደግነትህ በሕይወቴ እጅግ ስለበዛ አሳጣኸኝ ከቶ ምለው ከምሥጋና ሌላ (፪x)


አዝ

ምክንያቴ ብዙ ነው እጅግ ብዙ ብዙ

አጥንቶቼም በርቱ ለአምላኬ ተገዙ

ነፍሴ ሆይ አክብሪው ከሞት ያዳነሽን

ዝም አትበይ ተነሽ አመስግኝ ጌታሽን (፪x)


ከቶ አልሻም በዘመኔ ካንተ ሌላ ለኔ

ቆርጫለሁ ላልለይህ ኢየሱስ መድህኔ

ብቻ አንተ ክበር እንጂ ይሁን ደስ እንዳለህ

አልሰለችም ሁልጊዜ ጌታዬ ባከብርህ (፪x)


አዝ

ምክንያቴ ብዙ ነው እጅግ ብዙ ብዙ

አጥንቶቼም በርቱ ለአምላኬ ተገዙ

ነፍሴ ሆይ አክብሪው ከሞት ያዳነሽን

ዝም አትበይ ተነሽ አመስግኝ ጌታሽን (፪x)


ልማድህ ነው ከፍ ማድረግ ከብረህ የምታከብር

ትቢያ አራግፈህ መሸላለም ማብቃት ለቁም ነገር

ስንቱ አረፈ እፎይ አለ ወዳንተ ሲጠጋ

አመለጠ ባንተ ጉልበት ከጠላት መንጋጋ (፪x)


አዝ

ምክንያቴ ብዙ ነው እጅግ ብዙ ብዙ

አጥንቶቼም በርቱ ለአምላኬ ተገዙ

ነፍሴ ሆይ አክብሪው ከሞት ያዳነሽን

ዝም አትበይ ተነሽ አመስግኝ ጌታሽን (፪x)


በምስጋና ላይ ምስጋና ገና አበዛለሁ

ተባረክ ብዬ ሁልጊዜ መቼ እጠግባለሁ (፪x)


በዝማሬ ላይ ዝማሬ ገና አበዛለሁ

ተባረክ ብዬ ሁልጊዜ መቼ እጠግባለሁ (፪x)