Agegnehu Yideg/Bezu Yehonkelegn/Mesgana Mesgana

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ዘማሪ አገኘሁ ይደግ
ርዕስ ምሥጋና ምሥጋና

የውለታህን ልክ ቆጥሬ ቆጥሬ
መጨረስ አልቻልኩም ለአሕዛብ ተናግሬ
ያደረክልኝ ቆጥሬ ቆጥሬ
መጨረስ አልችልም በቤትህ ዘመሬ
ያደረክልኝ ቆጥሬ ቆጥሬ
መጨረስ አልችልም ለአሕዛብ ተናግሬ


ምሥጋና ምሥጋና ክብር (፪x)
ለአምላካችን ለእግዚአብሔር (፪x)
ኃጥያተኞች ሳለን እግዚአብሔር አሰበን
ከፋንዲያ ላይም ከፍ ከፍ አረገን
በሕይወት መዝገብ ላይ ሥማችንን ጻፈው
የዘለዓለም አምላክ ምሥጋና ይድረሰው
በሕይወት መዝገብ ላይ ሥማችንን ጻፈው
የናዝሬቱ ኢየሱስ ምሥጋና ይድረሰው።

አዝ

ኢየሱስ እረኛችን ጠባቂያችን ሆኗል
በሞት ጥላም ብንሄድ ምንድን ያስፈራናል?
በለመለምው መስክ በእረፍት ውኃ ዘንድ
ሁሌ ይመራናል ወደ እውነት መንገድ። (፪x)

አዝ

አዕምሮን የሚያልፍ ሰላሙን ሰጥቶናል
በጌታ በኢየሱስ ሁሌ ደስ ይለናል
ምድር ብትናውጥ አንዳች አንሆንም
የመረጠን አምላክ/ኢየሱስ/ፈጽሞ አይተወንም (፪x)

አዝ

እግዚአብሔር ከላይ በድንቅ ጐብኝቶናል
በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በእሳት አጥምቆናል
በመከራም ጊዜ እንደሰታለን
እንደ ዘንባባ ዛፍ እንለመልማለን
በመከራም ጊዜ እንደሰታለን
በሽምግልናችን እንለመልማለን።


ላመስግነው 3x
ጌታ ፍጹም ወደር የለው
ላመስግነው 3x
ውዴ ፍጹም ወደር የለው
ኢየሱስ ጌታ ነው 2x
እረ ማነው ማነው እሱን የሚመስለው
ኢየሱስ ጌታ ነው 2x
እረ ማነው ማነው ክብሩን የሚችለው
ላመስግነው 3x
ጌታ ፍጹም ወደር የለው