ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ከአዕምሮአችን ፡ በላይ (Mesgana Mesgana Keaemroachen Belay)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አዝ፦ ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ምሥጋና
ከዐዕምሮአችን ፡ በላይ ፡ ለሆነው ፡ ውለታ
ቆጥረን ፡ እስከማንደርስ ፡ ለበዛው ፡ ስጦታ
እናከብርሃለን ፡ ክበርልን ፡ ጌታ

አሳዳጃችን ፡ ከባሕር ፡ ሰጥሞ
ምድረ ፡ በዳችን ፡ ባንተ: ለምልሞ
ከያለንበት ፡ ተሰብስበናል
እኛም ፡ ሰው ፡ ሆነን ፡ ሰውን ፡ ማርከናል

አዝ፦ ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ምሥጋና
ከዐዕምሮአችን ፡ በላይ ፡ ለሆነው ፡ ውለታ
ቆጥረን ፡ እስከማንደርስ ፡ ለበዛው ፡ ስጦታ
እናከብርሃለን ፡ ክበርልን ፡ ጌታ

በሰው ፡ ልጅ ፡ ኃጢአት ፡ ምድርን ፡ ብትቀጣ
የመከራ ፡ ጐርፍ ፡ ከላይ ፡ ቢመጣ
በዙሪያችን ፡ አጥር ፡ ሰርተሃል
ለእኛ ፡ ለሕዝብህ ፡ መርከብ ፡ ሆነሃል

አዝ፦ ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ምሥጋና
ከአዕምሮአችን ፡ በላይ ፡ ለሆነው ፡ ውለታ
ቆጥረን ፡ እስከማንደርስ ፡ ለበዛው ፡ ስጦታ
እናከብርሃለን ፡ ክበርልን ፡ ጌታ

የፈርዖን ፡ ጦር ፡ ሕዝቡን ፡ አሳዶ
እርሱ ፡ ግን ፡ ቀረ ፡ ከባሕር ፡ ማዶ
እርስታችንን ፡ በድል ፡ ወርሰናል
በአንተ ፡ እረኝነት ፡ እዚህ ፡ ደርሰናል