ከእግርህ ፡ ስር ፡ መሆን (Kegreh Ser Mehon)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

በብዙ ፡ ነገር ፡ እንታወካለን
ኑሮን ፡ ልንገፋ ፡ እንጨነቃለን
በሥጋ ፡ በነፍስ ፡ አንባክናለን
አርፎ ፡ መቀመጥን ፡ ከአንተም ፡ አፍ ፡ መስማትን
ገና ፡ አሁን ፡ ተረዳን ፡ ሰምቶ ፡ መታዘዝን

አዝ፦ ከእግርህ ፡ ስር ፡ መሆን ፡ ግሩም ፡ ነው
ቃልህን ፡ መማር ፡ መልካም ፡ ነው
የማይጠፋም ፡ ዕድል ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ሆይ (፪x)

ሲስሙህ ፡ ደስ ፡ እንደሚልህ ፡ ጌታችን
የአውራ ፡ በግ ፡ ስብ ፡ ብንሰጥህ ፡ ከእጃችን
ምንም ፡ አያረካህ ፡ እንደ ፡ መስማታቻን
የእኛ ፡ ብቻ ፡ ይሰማ ፡ እያሉ ፡ መለፍለፍ
መስማትን ፡ ያግዳል ፡ ተናግሮ ፡ ዓለማረፍ

አዝ፦ ከእግርህ ፡ ስር ፡ መሆን ፡ ግሩም ፡ ነው
ቃልህን ፡ መማር ፡ መልካም ፡ ነው
የማይጠፋም ፡ ዕድል ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ሆይ (፪x)

ደቀ ፡ መዝሙርም ፡ ሳይሆን ፡ ከቶ ፡ ሳይማር
እራሱን ፡ የሚሻም ፡ ከሹመቱ ፡ ሲሻር
ብቻውን ፡ ሲቀር ፡ ያለ ፡ እንዳች ፡ አጋር
ተግሳጽን ፡ ያገኛን ፡ ጠቢብ ፡ አስተውሎ
ልማር ፡ አስቀድሜ ፡ ሩጫው ፡ ይቆይ ፡ ብሎ

አዝ፦ ከእግርህ ፡ ስር ፡ መሆን ፡ ግሩም ፡ ነው
ቃልህን ፡ መማር ፡ መልካም ፡ ነው
የማይጠፋም ፡ ዕድል ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ሆይ (፪x)