የተሰማው ወደ የተማሰው (እግዚአብሔር ፡ ይሄ ፡ ነው (Egziabhier Yehie New))

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አዝ፦ እጅግ ፡ ተቸግሬ ፡ ስማጸን ፡ አይተኸኝ
እኔ ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ነኝ ፡ አትፍራ ፡ እያልከኝ
በመጽናናት ፡ ሞልተህ ፡ ደስታን ፡ ታስታጥቀኛለህ
የልቤ ፡ አምላክ ፡ ሆይ ፡ የዘለዓለም ፡ ዕድል ፡ ፈንታዬ ፡ ነህ

እግዚአብሔር ፡ ይሄ ፡ ነው ፡ ተስፋ ፡ ያደረግሁት
ታማኝነቱን ፡ አይቼ ፡ እጄን ፡ ልቤን ፡ የሰጠሁት
ያላዋቂዎች ፡ ልቦና ፡ በሰዎች ፡ ተስፋ ፡ ያደርጋል
ግን ፡ እግዚአብሔር ፡ ብቻ ፡ ደህንነትን ፡ ያዘጋጃል

አዝ፦ እጅግ ፡ ተቸግሬ ፡ ስማጸን ፡ አይተኸኝ
እኔ ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ነኝ ፡ አትፍራ ፡ እያልከኝ
በመጽናናት ፡ ሞልተህ ፡ ደስታን ፡ ታስታጥቀኛለህ
የልቤ ፡ አምላክ ፡ ሆይ ፡ የዘለዓለም ፡ ዕድል ፡ ፈንታዬ ፡ ነህ

የተማሰው ፡ ጉድጓድ ፡ አፉን ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ አልዘጋም
ጉልበቴ ፡ ባለቀ ፡ ጊዜ ፡ ለብቻዬ ፡ አልተውከኝም
ስለ ፡ ትንሿ ፡ እምነቴ ፡ ከባላጋራ ፡ ተሟግተህ
የድል ፡ አምባ ፡ አስረገጥከኝ ፡ ውጊያውን ፡ ሁሉ ፡ ፈጽመህ

አዝ፦ እጅግ ፡ ተቸግሬ ፡ ስማጸን ፡ አይተኸኝ
እኔ ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ነኝ ፡ አትፍራ ፡ እያልከኝ
በመጽናናት ፡ ሞልተህ ፡ ደስታን ፡ ታስታጥቀኛለህ
የልቤ ፡ አምላክ ፡ ሆይ ፡ የዘለዓለም ፡ ዕድል ፡ ፈንታዬ ፡ ነህ

ምሥጋናዬን ፡ እያዜምኩኝ ፡ በአንተ ፡ ደስ ፡ ይለኛል
በከንቱ ፡ በሚጠሉኝ ፡ ፊት ፡ ሞገስ ፡ አጐናጽፈኸኛል
ዓለም ፡ ብትሰርዘኝም ፡ የሕይወት ፡ መዝገብ ፡ አውቆኛል
እስከመጨረሻው ፡ ድረስ ፡ ሕይወቴ ፡ በአንተ ፡ ይጸናል

አዝ፦ እጅግ ፡ ተቸግሬ ፡ ስማጸን ፡ አይተኸኝ
እኔ ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ነኝ ፡ አትፍራ ፡ እያልከኝ
በመጽናናት ፡ ሞልተህ ፡ ደስታን ፡ ታስታጥቀኛለህ
የልቤ ፡ አምላክ ፡ ሆይ ፡ የዘለዓለም ፡ ዕድል ፡ ፈንታዬ ፡ ነህ