ድሉ ፡ የጌታችን ፡ ነው (Delu Yegietachen New)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አዝ፦ ድሉ ፡ የጌታችን ፡ ነው
ድሉ ፡ የአምላካችን ፡ ነው ፡ ድሉ
ድሉ ፡ የጌታችን ፡ ነው
ጠላትን ፡ ረገጠ ፡ አርነት ፡ አወጀ
ለኛ፡ለልጆቹ፡ማረፊያ፡አዘጋጀ
ድሉ ፡ የጌታችን ፡ ነው

1. ከዲያብሎስ ፡ ወጥመድ ፡ ልንድን
በጌታችን ፡ ብርታት ፡ ተሞላን
እንግዲህ ፡ እንገስግስ ፡ አንተኛ
የኢየሱስ ፡ ነን ፡ እኛ

አዝ፦ ድሉ ፡ የጌታችን ፡ ነው


2. እሥራኤልን ፡ ከግብጽ ፡ ያወጣ
ፈርኦንን ፡ በባህር ፡ የቀጣ
ይህን ፡ ታዳጊ ፡ አምላክ ፡ አምነናል
በድል ፡ ይመራናል

አዝ፦ ድሉ ፡ የጌታችን ፡ ነው


3. ኢያሱ ፡ ጌዴዎንና ፡ ዳዊት
አብርሐምና ፡ ሙሴ ፡ የሞቱት
የእምነትና ፡ የጦር ፡ አርበኞች
የድል ፡ ምሣሌዎች

አዝ፦ ድሉ ፡ የጌታችን ፡ ነው


4. የጠላት ፡ ማሽካካት ፡ ድንፋታ
የሰልፍ ፡ የጦር ፡ ብዛት ፡ ጋጋታ
ለኃያሉ ፡ ኢየሱስ ፡ ምኑ ፡ ነው
ሁሉም ፡ በእጁ ፡ ነው

አዝ፦ አዝ፦ ድሉ ፡ የጌታችን ፡ ነው
ድሉ ፡ የአምላካችን ፡ ነው ፡ ድሉ
ድሉ ፡ የጌታችን ፡ ነው
ጠላትን ፡ ረገጠ ፡ አርነት ፡ አወጀ
ለኛ፡ለልጆቹ፡ማረፊያ፡አዘጋጀ
ድሉ ፡ የጌታችን ፡ ነው