አልሰለችም ፡ ሁልጊዜ ፡ ጌታን ፡ እባርከዋለሁ (Alselechem Hulgizie Gietan Ebarkalew)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አዝ፦ አልሰለችም ፡ ሁልጊዜ ፡ ጌታን ፡ እባርከዋለሁ
ምህረቱ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ነው ፡ ይህን ፡ ተረድቻለሁ (፪x)
ኦ ፡ ፍቅሩ ፡ ማርኮኛል (፪x)
ተማርኬአለሁ ፡ በኢየሱስ ፡ ሰላም ፡ አግኝቻለሁ (፪x)

1. ምህረቱ ፡ እጅግ ፡ ብዘ ፡ ነው ፡ ቸርነቱ ፡ ወደር ፡ የለው
ከዓመት ፡ ዓመት ፡ አይለወጥ ፡ ፍቅሩ ፡ ቋሚ ፡ ሁሌ ፡ ጽኑ ፡ ነው
ውዴ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ እንደ ፡ እርሱ ፡ ያለ ፡ ከየት ፡ አገኛለሁ
በእኔ ፡ ሊይ ፡ የገለጸውን ፡ መውደዱን ፡ ተረድቻለሁ

አዝ፦ አልሰለችም ፡ ሁልጊዜ ፡ ጌታን ፡ እባርከዋለሁ
ምህረቱ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ነው ፡ ይህን ፡ ተረድቻለሁ (፪x)
ኦ ፡ ፍቅሩ ፡ ማርኮኛል (፪x)
ተማርኬአለሁ ፡ በኢየሱስ ፡ ሰላም ፡ አግኝቻለሁ (፪x)

2. የአምላኬን ፡ ትህትናውን ፡ የዋህነቱን ፡ አይቼ
አብሬው ፡ ልኖር ፡ ወሰንሁኝ ፡ ልከተለው ፡ ሁሉን ፡ ትቼ
ወደ ፡ እርሱ ፡ መጥቶ ፡ ማን ፡ አፍሯል
ምስኪኑ ፡ ሰው ፡ ቀን ፡ ወጥቶለታል
ኅዘኑ ፡ ማቁ ፡ ተቀዶ ፡ እምባው ፡ ታብሶለት ፡ ይኖራል

አዝ፦ አልሰለችም ፡ ሁልጊዜ ፡ ጌታን ፡ እባርከዋለሁ
ምህረቱ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ነው ፡ ይህን ፡ ተረድቻለሁ (፪x)
ኦ ፡ ፍቅሩ ፡ ማርኮኛል (፪x)
ተማርኬአለሁ ፡ በኢየሱስ ፡ ሰላም ፡ አግኝቻለሁ (፪x)

3. ድንቅ ፡ የሆነለት ፡ ይዘምር ፡ አይቆጠብ ፡ ማዳኑን ፡ ያውራ
ብቻውን ፡ ትዓምር ፡ የሚያደርግ ፡ እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ የለምና
አንደበቶች ፡ ይከፈቱ ፡ የንጉሱን ፡ ምስጋና ፡ ያውሩ
ሰማይን ፡ ምድርን ፡ ለሠራ ፡ ሰዎች ፡ ሁሉ ፡ ክብርን ፡ ይስጡ