አቤቱ ፡ እናመሰግንሃለን (Abietu Enamesegenehalen)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

1. ከፍ ፡ ከፍ ፡ አድርገን ፡ አንተን ፡ አክብረን
ታላቅ ፡ ሥምህን ፡ ደጋግመን ፡ ጠርተን
የዝማሬአችን ፡ መስዋዕት ፡ ወጥቶ
ታሸተዋልህ ፡ ልክ ፡ እንደ ፡ ሽቶ

አዝ፦ አቤቱ ፡ እናመሰግንሃለን (፪x)
ሥምህን ፡ እንጠራለን (፪x)

2. የሚሰዋልኝ ፡ ለእኔ ፡ ምሥጋና
እርሱ ፡ ያከብረኛል ፡ ብለሃልና
እናም ፡ ወደናል ፡ ለማክበር ፡ አንተን
ከሁሉም ፡ በላይ ፡ ክበር ፡ ተመሥገን

አዝ፦ አቤቱ ፡ እናመሰግንሃለን (፪x)
ሥምህን ፡ እንጠራለን (፪x)

3. አንተ ፡ ከፍ ፡ በል ፡ ጠላት ፡ ተዋርዶ
እኛም ፡ እንስገድ ፡ በረከት ፡ ወርዶ
ካለ ፡ አንተ ፡ ለእኛ ፡ ማን ፡ አለንና
በሙሉ ፡ ኃይላችን ፡ ይኸው ፡ ምሥጋና

አዝ፦ አቤቱ ፡ እናመሰግንሃለን (፪x)
ሥምህን ፡ እንጠራለን (፪x)

4. ከሥሞች ፡ በላይ ፡ ታላቅ ፡ ሥም ፡ ይዘህ
በሰማይ ፡ ስፍራ ፡ በክብር ፡ ያለህ
አንተ ፡ ነህና ፡ ለእኛ ፡ ተስፋችን
ሥምህ ፡ ሲጠራ ፡ ስማን ፡ ጌታችን

አዝ፦ አቤቱ ፡ እናመሰግንሃለን (፪x)
ሥምህን ፡ እንጠራለን (፪x)

5. ብለን ፡ ስንጮህ ፡ አቤቱ ፡ አቤቱ
ፈጥነህ ፡ የምትሰማን ፡ ሃያል ፡ ነህ ፡ ብርቱ
ከዘለዓለም ፡ እስከ ፡ ዘለዓለም
በዕልልታ ፡ በሆታ ፡ ክበር ፡ ተመሥገን

አዝ፦ አቤቱ ፡ እናመሰግንሃለን (፪x)
ሥምህን ፡ እንጠራለን (፪x)