Azeb Hailu/Embi/Temesgen

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ


ጽድቅን እንዲያወራ ምላሴ: እንድትረካ እንድታርፍ ነፍሴ

የዋጀኸኝ አምላኬ መድህኔ: ከዚህች ዓለም አመጻ ኩነኔ

እንዳይረክስ በከንቱ ከንፈሬ: እንዳልጥለው ውድ እንቁውን ክብሬ

ዘመኔን በእጆችህ ያዝክና: አራመድከኝ በሕይወት ጐዳና

አዝ ተመስገን ተመስገን ተመስገን ልበልህ ደግሜ

ከኃጢአት በሽታ ተፈውሼ ባንተ ታክሜ (፪x)

እንድረዳ ማዳንህን እንዳውቀው: ልቦናዬን ወዳንተ የመለስከው

እንዳያልፈኝ የሕይወቴ መና: ህሊናዬን ለቃልህ አቀናህ

በረከሰው ዓለም የቀደስከኝ: በጽድቅ መንገድ ላይ የመራኸኝ

ከብዙዎች እኔ ተለይቼ: ዘምራለሁ መቅደስህ ገብቼ

አዝ ተመስገን ተመስገን ተመስገን ልበልህ ደግሜ

ከኃጢአት በሽታ ተፈውሼ ባንተ ታክሜ (፪x)

አልመኝም ከእንግዲህ ወደ ውጪ: ረክቻለሁ ጌታ አንተን መርጬ

የዓለምን ከንቱነት ኮተቷን: ንቄዋለሁ ከነማንነቷ

ወስኛለሁ ልኖር አስከብሬህ: ላፈራልህ ጣፋጭ መልካም ፍሬ

ደስ እንዲልህ ሁሌ በእኔ ጌታ: እገዛለሁ ፈቅጄ በደስታ

አዝ ተመስገን ተመስገን ተመስገን ልበልህ ደግሜ ከኃጢአት በሽታ ተፈውሼ ባንተ ታክሜ (፪x)