Azeb Hailu/Embi/Negerulegn Merdo

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ዘማሪአዜብ ኃይሉ ርዕስ ንገሩልኝ መርዶ አልበም እምቢ

ንገሩልኝ መርዶ ለዚያ ለጠላቴ ፣ ለጠላቴ ወጥመዱ ተሰብሮ ማምለጥ መፈታቴን ፣ መፈታቴን ዳግም ላያገኘኝ ላልገባ በእጁ ፣ በእጁ እግዚአብሔር አስቦኝ አዳነኝ በልጁ ፣ ኦ በልጁ

አመለጥኩት አመለጥኩት አመለጥኩት መሃላውን ቃልኪዳኑን አፈረስኩት አዲስ ኪዳን አደረግኩኝ ከኢየሱስ ጋራ በጐልጐታ ቀራንዮ በዚያ ተራራ (፪x)

የተተበተበው ሠንሰለት አስፈሪው የሕይወት ጨለማ በድንገት ጠፋ ገፈፍ አለ ከሰማይ አንድ ድምጽ ሰማ ሲተማመንብኝ ሲመካ ሲል አትወጣም ፍጹም ከእጆቼ የጌታዬ ፍቅር ማረከኝ ወጣሁኝ ሰይጣንን ከድቼ

ከሕይወትም ሕይወት ከክብርም ክብር መውጣት ከጨለማ ከሙታን መንደር ለሰው በዘመኑ ይሄም አለ ለካ መስፈሪያ የሌው ሰላም ከቶ የማይለካ

ንገሩልኝ መርዶ ለዚያ ለጠላቴ ፣ ለጠላቴ ወጥመዱ ተሰብሮ ማምለጥ መፈታቴን ፣ መፈታቴን ዳግም ላያገኘኝ ላልገባ በእጁ ፣ በእጁ እግዚአብሔር አስቦኝ አዳነኝ በልጁ ፣ ኦ በልጁ

አመለጥኩት አመለጥኩት አመለጥኩት መሃላውን ቃልኪዳኑን አፈረስኩት አዲስ ኪዳን አደረግኩኝ ከኢየሱስ ጋራ በጐልጐታ ቀራንዮ በዚያ ተራራ (፪x)

ከሰማያት የተላከውን የሕይወትን ጥሪ ደብዳቤ ከቶ እንዳልረዳ እንዳይገባኝ እንዳላስተውለው አንብቤ ባይኖቼ ላይ የተጋረደው የከበበኝ ያ የሞት ጥላ በቃሉ ጉልበት ተሰበረ በዙሪያዬ ብርሃን ሞላ

መኖርስ ካልቀረ ትርጉም ያለው ኑሮ ለዘላለም ተድላ ከጌታ ጋር አብሮ አሁን ገና ደላኝ አሁን ተመቸኝ ከሁሉ የበለጠ ጌታ ኢየሱስ ያዘኝ

ንገሩልኝ መርዶ ለዚያ ለጠላቴ ፣ ለጠላቴ ወጥመዱ ተሰብሮ ማምለጥ መፈታቴ ፣ መፈታቴን ዳግም ላያገኘኝ ላልገባ በእጁ ፣ በእጁ እግዚአብሔር አስቦኝ አዳነኝ በልጁ ፣ ኦ በልጁ

አመለጥኩት አመለጥኩት አመለጥኩት መሃላውን ቃልኪዳኑን አፈረስኩት አዲስ ኪዳን አደረግኩኝ ከኢየሱስ ጋራ በጐልጐታ ቀራንዮ በዚያ ተራራ (፪x)

የክብር አምላክ እግዚአብሔር ወደ ክብሩ አስጠግቶኛል ለዘለዓለም አይናጋም ብርቱ ቅጥር ሰርቶልኛል ሺህ ቢፎክር ሺህ ቢዝትብኝ ጠላቴ ከየት ያገኘኛል የመስቀል ጀግና ጌታ ኢየሱስ ከመረቡ አስመልጦኛል

ደሙ በጐበኔ ላይ ስለተቀባ የሞት መላእክተኛ ከቤቴ እንዳይገባ ይህ ለአምላኬ ደስታ መርዶ ለጠላቴ ሆኗል ለዘላለም (እሰይ) እኔ በማምለጤ