Azeb Hailu/Embi/Melas Hulu

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አላደርግም ፡ ለሌላ ፡ ስግደት ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ አባት (፪x)
አልችልም ፡ ለሌላ ፡ መንበርከክ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ አምላክ (፪x)
አላሰማም ፡ ለሌላ ፡ እልልታ ፡ ላንተ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ ይህ ፡ ጌታ (፪x)
እኔ ፡ አልሰዋም ፡ ለሌላ ፡ አምልኮ ፡ ለሥምህ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ እኮ (፪x)

አዝ፦ ምላስ ፡ ሁሉ ፡ ያንተን ፡ ክብር ፡ ይናገረው ፡ ያውራ (፪x)
ጉልበት ፡ ሁሉ ፡ ተንበርክኮ ፡ ይደነቅ ፡ በስራህ (፪x)


ባሕር ከፍለህ ሕዝብህን ማሻገርህን
የልጆችህን ጠላት በዚያ ማስጠምህን
በምድረ በዳው ላይ መናን ማውረድህን
ከደረቀው አለት ውሃ ማፍለቅህን

(ኦሆ) ፡ ታምራትህ ፡ (ኦሆ) ፡ ድንቅህን ፡ ሁሉ
(ኦሆ) ፡ ይናገረው ፡ (ኦሆ) ፡ ምላስ ፡ ሁሉ
(ኦሆ) ፡ ታምራትህን ፡ (ኦሆ) ፡ ድንቅህን ፡ ሁሉ
(ኦሆ) ፡ ይዘምረው ፡ (ኦሆ) ፡ ምላስ ፡ ሁሉ

አዝ፦ ምላስ ፡ ሁሉ ፡ ያንተን ፡ ክብር ፡ ይናገረው ፡ ያውራ (፪x)
ጉልበት ፡ ሁሉ ፡ ተንበርክኮ ፡ ይደነቅ ፡ በስራህ (፪x)

የማይፈወሰውን ፡ ደዌ ፡ ማዳንህን
የሞተውን ፡ ከመቃብር ፡ ማንሳትህን
ሁለት ፡ ዓሣ ፡ ለአምስት ፡ ሺህ ፡ ማጥገብህን
በውሃም ፡ ላይ ፡ መሄድ ፡ መጓዝ ፡ መቻልህን

(ኦሆ) ፡ ታምራትህ ፡ (ኦሆ) ፡ ድንቅህን ፡ ሁሉ
(ኦሆ) ፡ ይናገረው ፡ (ኦሆ) ፡ ምላስ ፡ ሁሉ
(ኦሆ) ፡ ታምራትህን ፡ (ኦሆ) ፡ ድንቅህን ፡ ሁሉ
(ኦሆ) ፡ ይዘምረው ፡ (ኦሆ) ፡ ምላስ ፡ ሁሉ

አዝ፦ ምላስ ፡ ሁሉ ፡ ያንተን ፡ ክብር ፡ ይናገረው ፡ ያውራ (፪x)
ጉልበት ፡ ሁሉ ፡ ተንበርክኮ ፡ ይደነቅ ፡ በስራህ (፪x)

ስለ ፡ ሰዎች ፡ ሃጥያት ፡ ራስህን ፡ መስጠትህን
በመስቀል ፡ ላይ ፡ ተቸንክረህ ፡ መሞትህን
ከሙታንም ፡ በኩር ፡ ሆነህ ፡ መውጣትህን
በአባትህ ፡ ቀኝ ፡ ኦ ፡ በክብር ፡ መሆንህን

(ኦሆ) ፡ ታምራትህ ፡ (ኦሆ) ፡ ድንቅህን ፡ ሁሉ
(ኦሆ) ፡ ይናገረው ፡ (ኦሆ) ፡ ምላስ ፡ ሁሉ
(ኦሆ) ፡ ታምራትህን ፡ (ኦሆ) ፡ ድንቅህን ፡ ሁሉ
(ኦሆ) ፡ ይመስክረው ፡ (ኦሆ) ፡ ምላስ ፡ ሁሉ (፪x)